ዮሐንስ 3:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ+ በልጁ የሚያምን* ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።+ ሮም 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።+ ሮም 8:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ለገዛ ልጁ እንኳ ያልሳሳው፣ ከዚህ ይልቅ ለእኛ ለሁላችን አሳልፎ የሰጠው+ አምላክ፣ ከእሱ ጋር አብሮ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ እንዴት በደግነት አይሰጠንም? 1 ዮሐንስ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ምሥክርነቱም ይህ ነው፤ አምላክ የዘላለም ሕይወት ሰጠን፤+ ይህም ሕይወት የተገኘው በልጁ ነው።+