ዘዳግም 34:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+ የሐዋርያት ሥራ 8:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሲሰሙ+ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው፤ የሐዋርያት ሥራ 8:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤+ እነሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። የሐዋርያት ሥራ 13:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነዚህ ይሖዋን* እያገለገሉና* እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ”+ አለ። 3 እነሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው። 1 ጢሞቴዎስ 4:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 የሽማግሌዎች አካል እጁን በአንተ ላይ በጫነበት+ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን ስጦታ ቸል አትበል። 1 ጢሞቴዎስ 5:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በማንም ሰው ላይ እጅህን ለመጫን አትቸኩል፤*+ እንዲሁም በሌሎች ኃጢአት ተካፋይ አትሁን፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ። 2 ጢሞቴዎስ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ በአንተ ላይ እጄን በጫንኩበት+ ጊዜ የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ በቅንዓት እንድትጠቀምበት* አሳስብሃለሁ።
9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+
2 እነዚህ ይሖዋን* እያገለገሉና* እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ”+ አለ። 3 እነሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው።