ዕብራውያን 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን*+ ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል”+ ይላል። ዕብራውያን 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?+ ራእይ 14:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል* ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር።+