ኢሳይያስ 11:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+ ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል። የሐዋርያት ሥራ 17:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 እርግጥ አምላክ ሰዎች ባለማወቅ የኖሩበትን ጊዜ+ ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ እያሳሰበ ነው። ሮም 10:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ምንም ልዩነት የለምና።+ የሁሉም ጌታ አንድ ነው፤ እሱም የሚለምኑትን ሁሉ አብዝቶ ይባርካል።* ሮም 15:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ክርስቶስ፣ አምላክ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ሲል ለተገረዙት አገልጋይ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤+ በተጨማሪም አገልጋይ የሆነው፣ አምላክ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለማረጋገጥ+ 9 እንዲሁም ብሔራት አምላክን ስለ ምሕረቱ ያከብሩት ዘንድ ነው።+ ይህም “ስለዚህ በብሔራት መካከል በይፋ አወድስሃለሁ፤ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+
8 ክርስቶስ፣ አምላክ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ሲል ለተገረዙት አገልጋይ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤+ በተጨማሪም አገልጋይ የሆነው፣ አምላክ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለማረጋገጥ+ 9 እንዲሁም ብሔራት አምላክን ስለ ምሕረቱ ያከብሩት ዘንድ ነው።+ ይህም “ስለዚህ በብሔራት መካከል በይፋ አወድስሃለሁ፤ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+