ማቴዎስ 23:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ የሐዋርያት ሥራ 14:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ሆኖም ያላመኑት አይሁዳውያን ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰዎች* በማነሳሳት በወንድሞች ላይ ጥላቻ እንዲያድርባቸው አደረጉ።+ የሐዋርያት ሥራ 14:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ሆኖም አይሁዳውያን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን አግባቡ፤+ ጳውሎስንም በድንጋይ ከወገሩት በኋላ የሞተ መስሏቸው ጎትተው ከከተማዋ አወጡት።+ የሐዋርያት ሥራ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ሆኖም አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው+ በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ።
34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+
5 ሆኖም አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው+ በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ።