የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 39:7-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 በኋላም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጣለችበት፤ እሷም “ከእኔ ጋር ተኛ” ትለው ጀመር። 8 እሱ ግን ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ የጌታውን ሚስት እንዲህ አላት፦ “ጌታዬ በዚህ ቤት በእኔ እጅ ስላለው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውንም ነገር ሁሉ በአደራ ሰጥቶኛል። 9 በዚህ ቤት ውስጥ ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ጌታዬ ከአንቺ በስተቀር ምንም ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ ይህን ያደረገውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን እጅግ መጥፎ ድርጊት በመፈጸም በአምላክ ላይ እንዴት ኃጢአት እሠራለሁ?”+

  • 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+

  • ኤፌሶን 5:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 እንደምታውቁትና በሚገባ እንደምትገነዘቡት ሴሰኛ*+ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ+ ማለትም ጣዖት አምላኪ የሆነ ማንኛውም ሰው በክርስቶስና በአምላክ መንግሥት ምንም ውርሻ የለውም።+

  • ቆላስይስ 3:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ስለዚህ በምድር ያሉትን የአካል ክፍሎቻችሁን ግደሉ፤+ እነሱም የፆታ ብልግና፣* ርኩሰት፣ ልቅ የሆነ የፍትወት ስሜት፣+ መጥፎ ፍላጎትና ጣዖት አምልኮ የሆነው ስግብግብነት ናቸው።

  • 1 ተሰሎንቄ 4:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 የአምላክ ፈቃድ እንድትቀደሱና+ ከፆታ ብልግና* እንድትርቁ ነው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ