-
1 ጢሞቴዎስ 3:1-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ይህ ቃል እምነት የሚጣልበት ነው፦ የበላይ ተመልካች+ ለመሆን የሚጣጣር ሰው መልካም ሥራን ይመኛል። 2 ስለዚህ የበላይ ተመልካች የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በልማዶቹ ልከኛ የሆነ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ሥርዓታማ፣ እንግዳ ተቀባይ፣+ የማስተማር ብቃት ያለው፣+ 3 የማይሰክር፣*+ ኃይለኛ ያልሆነ፣* ይልቁንም ምክንያታዊ የሆነ፣+ የማይጣላ፣+ ገንዘብ ወዳድ ያልሆነ፣+ 4 ታዛዥና ቁም ነገረኛ የሆኑ ልጆች ያሉትና የራሱን ቤተሰብ በተገቢው ሁኔታ የሚያስተዳድር ሊሆን ይገባዋል፤+ 5 (ደግሞስ አንድ ሰው የራሱን ቤተሰብ እንዴት እንደሚያስተዳድር ካላወቀ የአምላክን ጉባኤ እንዴት ሊንከባከብ ይችላል?) 6 በትዕቢት ተነፍቶ ዲያብሎስ የተፈረደበት ዓይነት ፍርድ እንዳይፈረድበት አዲስ ክርስቲያን አይሁን።+ 7 ከዚህም በተጨማሪ እንዳይነቀፍና* በዲያብሎስ ወጥመድ ውስጥ እንዳይወድቅ በውጭ ባሉት* ሰዎች ዘንድ በመልካም የተመሠከረለት* ሊሆን ይገባል።+
-
-
ቲቶ 1:5-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 አንተን በቀርጤስ የተውኩህ ያልተስተካከሉትን* ነገሮች እንድታስተካክልና በሰጠሁህ መመሪያ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፤ 6 ይኸውም ከክስ ነፃ የሆነ፣ የአንዲት ሚስት ባል እንዲሁም በስድነት* ወይም በዓመፀኝነት የማይከሰሱ አማኝ የሆኑ ልጆች ያሉት ማንም ሰው ካለ እንድትሾም ነው።+ 7 ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣+ ግልፍተኛ፣+ ሰካራም፣ ኃይለኛና* አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤ 8 ከዚህ ይልቅ እንግዳ ተቀባይ፣+ ጥሩ የሆነውን ነገር የሚወድ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ጻድቅ፣ ታማኝ፣+ ራሱን የሚገዛ፣+ 9 እንዲሁም ትክክለኛ* በሆነው ትምህርት+ ማበረታታትም* ሆነ ይህን ትምህርት የሚቃወሙትን መውቀስ+ ይችል ዘንድ የማስተማር ጥበቡን+ ሲጠቀም የታመነውን ቃል* በጥብቅ የሚከተል ሊሆን ይገባል።
-