ዘፍጥረት 9:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ብቻ ሕይወቱ* ማለትም ደሙ+ በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።+ ዘሌዋውያን 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’” ዘሌዋውያን 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 1 ሳሙኤል 14:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ስለሆነም ሕዝቡ ምርኮውን በመስገብገብ ተሻምቶ ወሰደ፤ በጎችን፣ ከብቶችንና ጥጆችን ወስደው መሬት ላይ አረዷቸው፤ ሥጋውንም ከነደሙ በሉት።+ 33 በመሆኑም ሳኦል “ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት+ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው” ተብሎ ተነገረው። እሱም በዚህ ጊዜ “እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል። በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ” አለ።
10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
32 ስለሆነም ሕዝቡ ምርኮውን በመስገብገብ ተሻምቶ ወሰደ፤ በጎችን፣ ከብቶችንና ጥጆችን ወስደው መሬት ላይ አረዷቸው፤ ሥጋውንም ከነደሙ በሉት።+ 33 በመሆኑም ሳኦል “ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት+ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው” ተብሎ ተነገረው። እሱም በዚህ ጊዜ “እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል። በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ” አለ።