ዘፍጥረት 9:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ብቻ ሕይወቱ* ማለትም ደሙ+ በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።+ ዘሌዋውያን 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። ዘሌዋውያን 17:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 “‘አንድ እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው ለመብልነት የተፈቀደ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን ያፍሰው፤+ አፈርም ያልብሰው። ዘዳግም 12:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ብቻ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ፤+ ምክንያቱም ደም ሕይወት* ነው፤+ ሕይወትን* ደግሞ ከሥጋ ጋር መብላት የለብህም። የሐዋርያት ሥራ 15:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚህ ይልቅ በጣዖት+ ከረከሱ ነገሮች፣ ከፆታ ብልግና፣*+ ታንቆ ከሞተ* እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከደም እንዲርቁ+ እንጻፍላቸው። የሐዋርያት ሥራ 15:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ እንስሳ* ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* ራቁ።+ ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!”*
10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
13 “‘አንድ እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው ለመብልነት የተፈቀደ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን ያፍሰው፤+ አፈርም ያልብሰው።
29 ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ እንስሳ* ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* ራቁ።+ ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!”*