ማቴዎስ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲነቅፏችሁ፣+ ስደት ሲያደርሱባችሁና+ ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲያስወሩባችሁ ደስተኞች ናችሁ።+ የሐዋርያት ሥራ 16:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚያም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፦ “እነዚህ ሰዎች ከተማችንን ክፉኛ እያወኩ ነው።+ እነሱ አይሁዳውያን ናቸው፤ 21 ደግሞም እኛ ሮማውያን ልንቀበለውም ሆነ ልንፈጽመው የማይገባንን ልማድ እያስፋፉ ነው።” የሐዋርያት ሥራ 17:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ “ዓለምን ሁሉ ያናወጡት* እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤+ 7 ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።”+
20 ከዚያም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፦ “እነዚህ ሰዎች ከተማችንን ክፉኛ እያወኩ ነው።+ እነሱ አይሁዳውያን ናቸው፤ 21 ደግሞም እኛ ሮማውያን ልንቀበለውም ሆነ ልንፈጽመው የማይገባንን ልማድ እያስፋፉ ነው።”
6 ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ “ዓለምን ሁሉ ያናወጡት* እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤+ 7 ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።”+