ኢሳይያስ 26:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።* ማቴዎስ 22:31, 32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 የሙታንን ትንሣኤ በተመለከተ አምላክ እንዲህ ሲል ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁም? 32 ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ብሏል።+ እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”+ ሉቃስ 14:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ 14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።” ዮሐንስ 5:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+ ዮሐንስ 11:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ።+ በእኔ የሚያምን* ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል፤ ዕብራውያን 11:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤+ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው። ራእይ 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው።+ ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+
19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።*
31 የሙታንን ትንሣኤ በተመለከተ አምላክ እንዲህ ሲል ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁም? 32 ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ብሏል።+ እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”+
13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ 14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።”
28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+
35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤+ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው።
12 ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው።+ ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+