መዝሙር 18:49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 ይሖዋ ሆይ፣ በብሔራት መካከል የማከብርህ ለዚህ ነው፤+ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ ኢሳይያስ 11:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+ ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል። ሉቃስ 2:30-32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ 31 ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤+ 32 ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ+ የሚገልጥ ብርሃን+ እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።”
30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ 31 ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤+ 32 ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ+ የሚገልጥ ብርሃን+ እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።”