ዮሐንስ 5:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ኢየሱስም “ተነስ! ምንጣፍህን* ተሸክመህ ሂድ” አለው።+ 9 ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም* አንስቶ መሄድ ጀመረ። ቀኑም ሰንበት ነበር። የሐዋርያት ሥራ 9:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ጴጥሮስም “ኤንያስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል።+ ተነሳና አልጋህን አንጥፍ” አለው።+ እሱም ወዲያውኑ ተነሳ። የሐዋርያት ሥራ 14:8-10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በልስጥራም አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። እሱም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሲሆን ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያዳምጥ ነበር። ጳውሎስም ትኩር ብሎ አየውና ለመዳን የሚያበቃ እምነት እንዳለው ተመልክቶ+ 10 ከፍ ባለ ድምፅ “ተነስና በእግርህ ቁም” አለው። ሰውየውም ዘሎ ተነሳና መራመድ ጀመረ።+
8 በልስጥራም አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። እሱም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሲሆን ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያዳምጥ ነበር። ጳውሎስም ትኩር ብሎ አየውና ለመዳን የሚያበቃ እምነት እንዳለው ተመልክቶ+ 10 ከፍ ባለ ድምፅ “ተነስና በእግርህ ቁም” አለው። ሰውየውም ዘሎ ተነሳና መራመድ ጀመረ።+