11 በእሱ ላይ ከደረሰው ሥቃይ የተነሳ፣ በሚያየው መልካም ነገር ይደሰታል።
ጻድቅ አገልጋዬ+ በእውቀቱ አማካኝነት
ብዙ ሰዎች ጻድቅ ሆነው እንዲቆጠሩ ይረዳል፤+
በደላቸውንም ይሸከማል።+
12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤
ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤
ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+
ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+
የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+
ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+