ዘሌዋውያን 18:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ሉቃስ 10:26-28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። 28 ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው።+
26 ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። 28 ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው።+