ኤርምያስ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ? የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+ የሐዋርያት ሥራ 17:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች+ ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።+