ዮሐንስ 1:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ስላመኑ+ የአምላክ ልጆች+ የመሆን መብት ሰጣቸው። ገላትያ 3:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 እንደ እውነቱ ከሆነ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባላችሁ እምነት የተነሳ+ የአምላክ ልጆች ናችሁ።+ 1 ዮሐንስ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እኛ አሁን የአምላክ ልጆች ነን፤+ ሆኖም ወደፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም።+ እሱ በሚገለጥበት ጊዜ እንደ እሱ እንደምንሆን እናውቃለን፤ ምክንያቱም እሱን በእርግጥ እናየዋለን።
2 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እኛ አሁን የአምላክ ልጆች ነን፤+ ሆኖም ወደፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም።+ እሱ በሚገለጥበት ጊዜ እንደ እሱ እንደምንሆን እናውቃለን፤ ምክንያቱም እሱን በእርግጥ እናየዋለን።