ሮም 8:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ዳግመኛ ለፍርሃት የሚዳርጋችሁን የባርነት መንፈስ አልተቀበላችሁም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስዳችሁ የሚያስችል መንፈስ አግኝታችኋል፤ ይህም መንፈስ “አባ፣* አባት!”+ ብለን እንድንጣራ ይገፋፋናል። 16 የአምላክ ልጆች+ መሆናችንን ይህ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሠክራል።+ ኤፌሶን 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ደግሞም እሱ እንደወደደና እንደ በጎ ፈቃዱ+ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የገዛ ራሱ ልጆች አድርጎ ሊወስደን+ አስቀድሞ ወስኗል፤+
15 ዳግመኛ ለፍርሃት የሚዳርጋችሁን የባርነት መንፈስ አልተቀበላችሁም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስዳችሁ የሚያስችል መንፈስ አግኝታችኋል፤ ይህም መንፈስ “አባ፣* አባት!”+ ብለን እንድንጣራ ይገፋፋናል። 16 የአምላክ ልጆች+ መሆናችንን ይህ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሠክራል።+