ሉቃስ 17:29, 30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ሆኖም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ከሰማይ እሳትና ድኝ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው።+ 30 የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን+ እንዲሁ ይሆናል። 2 ተሰሎንቄ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 መከራን የምትቀበሉት እናንተ ግን ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር+ ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ+ ከእኛ ጋር እረፍት ይሰጣችኋል፤ 1 ጴጥሮስ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እነዚህ ፈተናዎች የሚደርሱባችሁ፣ በእሳት የተፈተነ ቢሆንም እንኳ ሊጠፋ ከሚችለው ወርቅ እጅግ የላቀ ዋጋ ያለውና ተፈትኖ* የተረጋገጠው እምነታችሁ+ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ግርማንና ክብርን ያስገኝ ዘንድ ነው።+
7 እነዚህ ፈተናዎች የሚደርሱባችሁ፣ በእሳት የተፈተነ ቢሆንም እንኳ ሊጠፋ ከሚችለው ወርቅ እጅግ የላቀ ዋጋ ያለውና ተፈትኖ* የተረጋገጠው እምነታችሁ+ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ግርማንና ክብርን ያስገኝ ዘንድ ነው።+