30 እንግዲህ ወንድሞች፣ ስለ እኔ አምላክን በመለመን ከእኔ ጋር አብራችሁ በጸሎት እንድትተጉ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከመንፈስ በሚገኘው ፍቅር አበረታታችኋለሁ፤ 31 በይሁዳ ካሉት የማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና+ በኢየሩሳሌም ለሚገኙት ቅዱሳን+ የማቀርበው አገልግሎት በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤ 32 ይኸውም አምላክ ከፈቀደ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተ ጋር በመሆን መንፈሴ እንዲታደስ ነው።