ምሳሌ 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 አንዱ በልግስና ይሰጣል፤* ሆኖም ተጨማሪ ያገኛል፤+ሌላው ደግሞ ለመስጠት ይሰስታል፤ ነገር ግን ለድህነት ይዳረጋል።+ ምሳሌ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ ምሳሌ 22:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለጋስ ሰው* ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና።+ መክብብ 11:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል፤*+ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።+ ሉቃስ 6:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”
38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”