ማርቆስ 2:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው+ ከእነሱ ጋር እያለ ጓደኞቹ የሚጾሙበት ምን ምክንያት አለ? ሙሽራው አብሯቸው እስካለ ድረስ ሊጾሙ አይችሉም። ኤፌሶን 5:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ምክንያቱም ክርስቶስ አካሉ ለሆነውና አዳኙ ለሆነለት ጉባኤ ራስ እንደሆነ+ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነው።+ ራእይ 21:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ደግሞም ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤+ እሷም ለባሏ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ነበር።+ ራእይ 21:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች የተሞሉትን ሰባቱን ሳህኖች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት+ አንዱ መጥቶ “ና፣ የበጉን ሚስት፣ ሙሽራይቱን+ አሳይሃለሁ” አለኝ።