ዘሌዋውያን 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ማቴዎስ 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “እንግዲህ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው።+ ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል የሚሉት ይህንኑ ነው።+ ማቴዎስ 22:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ሁለተኛውም ይህንኑ የሚመስል ሲሆን ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል።+ ሮም 13:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እርስ በርስ ከመዋደድ በቀር በማንም ላይ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤+ ሰውን የሚወድ ሁሉ ሕጉን ፈጽሟልና።+ 9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል። ያዕቆብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው።
8 እርስ በርስ ከመዋደድ በቀር በማንም ላይ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤+ ሰውን የሚወድ ሁሉ ሕጉን ፈጽሟልና።+ 9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል።