ማቴዎስ 28:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው፦ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።+ ኤፌሶን 5:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ምክንያቱም ክርስቶስ አካሉ ለሆነውና አዳኙ ለሆነለት ጉባኤ ራስ እንደሆነ+ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነው።+ ቆላስይስ 1:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እሱ የአካሉ ማለትም የጉባኤው ራስ ነው።+ በሁሉም ነገር ቀዳሚ መሆን እንዲችልም እሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኩር ነው፤+