9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ 11 አንዳንዶቻችሁም እንደዚህ ነበራችሁ። ሆኖም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችሁ ነጽታችኋል፣+ ተቀድሳችኋል+ እንዲሁም ጻድቃን ተብላችኋል።+