የሐዋርያት ሥራ 8:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሳኦልም በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ ጀመረ። በየቤቱ እየገባ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ጎትቶ በማውጣት ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።+ የሐዋርያት ሥራ 9:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ 2 የጌታን መንገድ የሚከተሉትን+ በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው። ገላትያ 1:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በእርግጥ፣ በአይሁዳውያን ሃይማኖት+ ሳለሁ ምን ዓይነት ሰው እንደነበርኩ ሰምታችኋል፤ የአምላክን ጉባኤ ክፉኛ* አሳድድና ለማጥፋት ጥረት አደርግ ነበር፤+ ፊልጵስዩስ 3:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝኩና+ ከእስራኤል ብሔር፣ ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ስሆን ከዕብራውያን የተወለድኩ ዕብራዊ ነኝ፤+ ስለ ሕግ ከተነሳ ፈሪሳዊ ነበርኩ፤+ 6 ስለ ቅንዓት ከተነሳ በጉባኤው ላይ ስደት አደርስ ነበር፤+ ሕጉን በመታዘዝ ስለሚገኘው ጽድቅ ከተነሳ ደግሞ እንከን የማይገኝብኝ መሆኔን አስመሥክሬአለሁ።
9 ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ 2 የጌታን መንገድ የሚከተሉትን+ በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው።
5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝኩና+ ከእስራኤል ብሔር፣ ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ስሆን ከዕብራውያን የተወለድኩ ዕብራዊ ነኝ፤+ ስለ ሕግ ከተነሳ ፈሪሳዊ ነበርኩ፤+ 6 ስለ ቅንዓት ከተነሳ በጉባኤው ላይ ስደት አደርስ ነበር፤+ ሕጉን በመታዘዝ ስለሚገኘው ጽድቅ ከተነሳ ደግሞ እንከን የማይገኝብኝ መሆኔን አስመሥክሬአለሁ።