ዘፍጥረት 21:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ሲወለድ ዕድሜው 100 ዓመት ነበር። ዘፍጥረት 22:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+ 1 ነገሥት 4:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ይሁዳና እስራኤል ከብዛታቸው የተነሳ እንደ ባሕር አሸዋ ነበሩ፤+ እነሱም ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ነበር።+