-
ዕብራውያን 10:19-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅዱሱ ስፍራ በሚወስደው መንገድ ለመግባት የሚያስችል ድፍረት* አግኝተናል፤+ 20 እሱ የከፈተልን* ይህ መንገድ ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ ነው። ይህን ያደረገው በመጋረጃው+ ማለትም በሥጋው በኩል በማለፍ ነው፤ 21 በተጨማሪም በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን+ 22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት+ ልባችንን ተረጭተን እንዲሁም ሰውነታችንን በንጹሕ ውኃ ታጥበን+ በቅን ልቦና እና በሙሉ እምነት ወደ አምላክ እንቅረብ።
-