17 ስለዚህ አሕዛብ በአእምሯቸው ከንቱነት+ እንደሚመላለሱ እናንተም ከእንግዲህ እንዳትመላለሱ በጌታ እናገራለሁ እንዲሁም እመሠክራለሁ።+ 18 እነሱ በውስጣቸው ካለው ድንቁርናና ከልባቸው መደንደን የተነሳ አእምሯቸው ጨልሟል፤ እንዲሁም ከአምላክ ከሚገኘው ሕይወት ርቀዋል። 19 የሥነ ምግባር ስሜታቸው ስለደነዘዘ በስግብግብነት ማንኛውንም ዓይነት ርኩሰት ለመፈጸም ራሳቸውን ማንአለብኝነት ለሚንጸባረቅበት ድርጊት+ አሳልፈው ሰጥተዋል።