ዮሐንስ 3:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ አንድ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ*+ በቀር የአምላክን መንግሥት ሊያይ አይችልም”+ አለው። 2 ቆሮንቶስ 5:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በመሆኑም ማንም ከክርስቶስ ጋር አንድነት ካለው አዲስ ፍጥረት ነው፤+ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፤ እነሆ፣ አዳዲስ ነገሮች ወደ ሕልውና መጥተዋል! 1 ጴጥሮስ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤ እሱ በታላቅ ምሕረቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ+ አማካኝነት ለሕያው ተስፋ+ እንደ አዲስ ወልዶናልና፤+ 1 ዮሐንስ 3:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከአምላክ የተወለደ ሁሉ በኃጢአት ጎዳና አይመላለስም፤+ የአምላክ ዘር* እንዲህ ባለው ሰው ውስጥ ይኖራልና፤ በኃጢአት ጎዳናም ሊመላለስ አይችልም፤ ይህ ሰው ከአምላክ የተወለደ ነውና።+
9 ከአምላክ የተወለደ ሁሉ በኃጢአት ጎዳና አይመላለስም፤+ የአምላክ ዘር* እንዲህ ባለው ሰው ውስጥ ይኖራልና፤ በኃጢአት ጎዳናም ሊመላለስ አይችልም፤ ይህ ሰው ከአምላክ የተወለደ ነውና።+