የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 22:5, 6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 እሱም የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞችን ላከ፤ በለዓም የሚኖረው በትውልድ አገሩ ባለው ወንዝ* ዳር በምትገኘው በጰቶር ነበር።+ እንዲህም ብለው እንዲነግሩት ላካቸው፦ “ከግብፅ ወጥቶ የመጣ አንድ ሕዝብ አለ። ይኸው የምድሪቱን* ገጽ* ሸፍኗል፤+ ደግሞም መጥቶ አፍንጫዬ ሥር ሰፍሯል። 6 እነሱ ከእኔ ይልቅ ኃያላን ስለሆኑ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።+ ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ፤ ምክንያቱም አንተ የባረክኸው ሁሉ የተባረከ፣ የረገምከውም ሁሉ የተረገመ እንደሚሆን በሚገባ አውቃለሁ።”

  • ዘኁልቁ 22:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 በመሆኑም የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ወደ በለዓም+ ሄዱ፤ የባላቅንም መልእክት ነገሩት።

  • ነህምያ 13:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 ይህም የሆነው ለእስራኤላውያን ምግብና ውኃ በመስጠት ፋንታ እነሱን እንዲረግምላቸው በለዓምን ቀጥረው ስለነበር ነው።+ ይሁንና አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።+

  • ይሁዳ 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በቃየን+ መንገድ ስለሄዱ፣ ለጥቅም ሲሉ የበለዓምን+ የተሳሳተ መንገድ በጭፍን ስለተከተሉና በቆሬ+ የዓመፅ ንግግር+ ስለጠፉ ወዮላቸው!

  • ራእይ 2:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 “‘ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገሮች አሉኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዉ ነገሮችን እንዲበሉና የፆታ ብልግና* እንዲፈጽሙ+ በፊታቸው ማሰናከያ እንዲያስቀምጥ ባላቅን+ ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት+ አጥብቀው የሚከተሉ በመካከልህ አሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ