ዘኁልቁ 31:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 የበለዓምን ቃል ሰምተው እስራኤላውያን በፌጎር በተከሰተው ነገር+ የተነሳ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጽሙ ያሳቷቸውና+ በዚህም ምክንያት በይሖዋ ማኅበረሰብ ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ ያደረጉት እነሱ አይደሉም?+ 2 ጴጥሮስ 2:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ቀናውን መንገድ ትተው በተሳሳተ ጎዳና ሄደዋል። ለጥቅም ሲል ክፉ ድርጊት መፈጸም የመረጠውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለዋል።+ ይሁዳ 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በቃየን+ መንገድ ስለሄዱ፣ ለጥቅም ሲሉ የበለዓምን+ የተሳሳተ መንገድ በጭፍን ስለተከተሉና በቆሬ+ የዓመፅ ንግግር+ ስለጠፉ ወዮላቸው!
16 የበለዓምን ቃል ሰምተው እስራኤላውያን በፌጎር በተከሰተው ነገር+ የተነሳ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጽሙ ያሳቷቸውና+ በዚህም ምክንያት በይሖዋ ማኅበረሰብ ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ ያደረጉት እነሱ አይደሉም?+