ዘዳግም 15:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* ሉቃስ 3:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እሱም መልሶ “ሁለት ልብስ* ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” አላቸው።+ ሮም 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ለቅዱሳን እንደየችግራቸው ያላችሁን አካፍሉ።+ የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል አዳብሩ።+ ያዕቆብ 2:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና* ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ 16 ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?+ 1 ዮሐንስ 4:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ማንም “አምላክን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን የሚጠላ ከሆነ ይህ ሰው ውሸታም ነው።+ ያየውን ወንድሙን የማይወድ+ ያላየውን አምላክ ሊወድ አይችልምና።+
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ 8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።*
15 አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና* ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ 16 ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?+