ማቴዎስ 24:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣+ ይገድሏችኋል+ እንዲሁም በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።+ ማቴዎስ 24:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤+ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል። ዮሐንስ 18:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው።+ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው።+ ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።” ራእይ 17:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እኔም ሴቲቱ በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምሥክሮች ደም ሰክራ አየኋት።+ ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅኩ። ራእይ 20:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+
37 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው።+ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው።+ ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።”
4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+