1 ዜና መዋዕል 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም ሰይጣን* እስራኤልን ለማጥቃት ቆርጦ ተነሳ፤ ደግሞም እስራኤልን እንዲቆጥር ዳዊትን አነሳሳው።+ ኢዮብ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የእውነተኛው አምላክ ልጆች*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም+ መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።+ ዘካርያስ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤+ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው+ ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?” ማቴዎስ 4:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤+ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’+ ተብሎ ተጽፏልና” አለው። ዮሐንስ 13:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት።+ ስለዚህ ኢየሱስ “እያደረግከው ያለኸውን ነገር ቶሎ አድርገው” አለው። 2 ተሰሎንቄ 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሆኖም የዓመፀኛው መገኘት የሰይጣን ሥራ+ ሲሆን ይህም የሚፈጸመው በተአምራት፣ በሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሁሉ+
2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤+ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው+ ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?”