መዝሙር 5:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ውሸት የሚናገሩትን ታጠፋለህ።+ ይሖዋ ዓመፀኞችንና አታላዮችን* ይጸየፋል።+ ኢሳይያስ 52:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 ጽዮን ሆይ፣+ ተነሺ! ተነሺ! ብርታትን ልበሺ!+ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ የሚያምሩ ልብሶችሽን ልበሺ!+ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዘና ርኩስ የሆነ ወደ አንቺ አይገባምና።+ 1 ቆሮንቶስ 6:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ ገላትያ 5:19-21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የሥጋ ሥራዎች በግልጽ የታወቁ ናቸው፤ እነሱም፦ የፆታ ብልግና፣*+ ርኩሰት፣ ማንአለብኝነት፣*+ 20 ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊት፣*+ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ ጭቅጭቅ፣ መከፋፈል፣ መናፍቅነት፣ 21 ምቀኝነት፣ ሰካራምነት፣+ መረን የለቀቀ ፈንጠዝያና እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው።+ እነዚህን በተመለከተ አስቀድሜ እንዳስጠነቀቅኳችሁ ሁሉ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ* የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ ራእይ 21:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣+ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣+ የሴሰኞች፣*+ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች+ ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው።+ ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።”+
52 ጽዮን ሆይ፣+ ተነሺ! ተነሺ! ብርታትን ልበሺ!+ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ የሚያምሩ ልብሶችሽን ልበሺ!+ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዘና ርኩስ የሆነ ወደ አንቺ አይገባምና።+
9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ 10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+
19 የሥጋ ሥራዎች በግልጽ የታወቁ ናቸው፤ እነሱም፦ የፆታ ብልግና፣*+ ርኩሰት፣ ማንአለብኝነት፣*+ 20 ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊት፣*+ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ ጭቅጭቅ፣ መከፋፈል፣ መናፍቅነት፣ 21 ምቀኝነት፣ ሰካራምነት፣+ መረን የለቀቀ ፈንጠዝያና እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው።+ እነዚህን በተመለከተ አስቀድሜ እንዳስጠነቀቅኳችሁ ሁሉ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ* የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+
8 ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣+ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣+ የሴሰኞች፣*+ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች+ ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው።+ ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።”+