43 አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ፤+
ከከዳተኛ ብሔር ጋር ያለብኝን ሙግት አንተ ተሟገትልኝ።+
አታላይና ዓመፀኛ ከሆነ ሰው ታደገኝ።
2 አንተ አምላኬና ምሽጌ ነህና።+
ለምን ተውከኝ?
ጠላቴ ከሚያደርስብኝ ጭቆና የተነሳ ለምን አዝኜ ልመላለስ?+
3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ።+
እነሱ ይምሩኝ፤+
ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ።+
4 ከዚያም ወደ አምላክ መሠዊያ፣+
እጅግ ሐሴት ወደማደርግበት አምላክ እመጣለሁ።
ደግሞም አምላክ ሆይ፣ አምላኬ፣ በበገና አወድስሃለሁ።+
5 ተስፋ የምቆርጠው ለምንድን ነው?
ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው?
አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+
እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+