የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 141
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • ጥበቃ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

        • ‘ጸሎቴ እንደ ዕጣን ይሁን’ (2)

        • የጻድቅ ወቀሳ እንደ ዘይት ነው (5)

        • ‘ክፉዎች የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ’ (10)

መዝሙር 141:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 31:17
  • +መዝ 40:13፤ 70:5
  • +መዝ 39:12

መዝሙር 141:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:34-36፤ ሉቃስ 1:9, 10፤ ራእይ 5:8፤ 8:3, 4
  • +ዘፀ 29:41

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    7/2022፣ ገጽ 20

    3/2022፣ ገጽ 21

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2014፣ ገጽ 16

    1/15/1999፣ ገጽ 10

መዝሙር 141:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 13:3፤ 21:23፤ ያዕ 1:26

መዝሙር 141:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:58፤ መዝ 119:36

መዝሙር 141:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:7, 9፤ ምሳሌ 17:10፤ ገላ 6:1
  • +ምሳሌ 6:23፤ ያዕ 5:14
  • +ምሳሌ 9:8፤ 19:25፤ 25:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 57

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2015፣ ገጽ 31

መዝሙር 141:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

መዝሙር 141:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴንም አታፍስሳት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 20:12፤ መዝ 25:15

መዝሙር 141:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አስ 7:10፤ መዝ 7:14, 15፤ 9:15፤ 57:6

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 141:1መዝ 31:17
መዝ. 141:1መዝ 40:13፤ 70:5
መዝ. 141:1መዝ 39:12
መዝ. 141:2ዘፀ 30:34-36፤ ሉቃስ 1:9, 10፤ ራእይ 5:8፤ 8:3, 4
መዝ. 141:2ዘፀ 29:41
መዝ. 141:3ምሳሌ 13:3፤ 21:23፤ ያዕ 1:26
መዝ. 141:41ነገ 8:58፤ መዝ 119:36
መዝ. 141:52ሳሙ 12:7, 9፤ ምሳሌ 17:10፤ ገላ 6:1
መዝ. 141:5ምሳሌ 6:23፤ ያዕ 5:14
መዝ. 141:5ምሳሌ 9:8፤ 19:25፤ 25:12
መዝ. 141:82ዜና 20:12፤ መዝ 25:15
መዝ. 141:10አስ 7:10፤ መዝ 7:14, 15፤ 9:15፤ 57:6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 141:1-10

መዝሙር

የዳዊት ማህሌት።

141 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ።+

እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ።+

አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።+

 2 ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+

የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+

 3 ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤

በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።+

 4 ከክፉ ሰዎች ጋር መጥፎ ድርጊት እንዳልፈጽም፣

ልቤ ወደ ክፉ ነገር እንዲያዘነብል አትፍቀድ፤+

ጣፋጭ ከሆነው ምግባቸው አልቋደስ።

 5 ጻድቅ ቢመታኝ፣ የታማኝ ፍቅር መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+

ቢወቅሰኝ በራስ ላይ እንደሚፈስ ዘይት አድርጌ አየዋለሁ፤+

ራሴም ይህን ፈጽሞ እንቢ አይልም።+

መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ።

 6 ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣

ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና።

 7 ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣

አጥንቶቻችንም በመቃብር* አፍ ላይ ተበታተኑ።

 8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ።+

አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።

ሕይወቴን አትውሰድ።*

 9 ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣

ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ።

10 ክፉዎች አንድ ላይ የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤+

እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ