የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ጎቶልያ በጉልበት ዙፋኑን ያዘች (1-3)

      • ኢዮዓስ በድብቅ እንዲነግሥ ተደረገ (4-12)

      • ጎቶልያ ተገደለች (13-16)

      • ዮዳሄ የወሰደው የተሃድሶ እርምጃ (17-21)

2 ነገሥት 11:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የመንግሥቱን ዘር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:26፤ 11:20፤ 2ዜና 21:5, 6፤ 24:7
  • +2ነገ 9:27
  • +2ዜና 21:4፤ 22:10-12

2 ነገሥት 11:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 12:1

2 ነገሥት 11:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሯጮቹን።”

  • *

    ወይም “ቃል ኪዳን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:27
  • +2ዜና 23:1-3

2 ነገሥት 11:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:1፤ 2ዜና 23:4-7

2 ነገሥት 11:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሚወጣበትም ሆነ በሚገባበት ጊዜ።”

2 ነገሥት 11:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:4
  • +2ዜና 23:8-11

2 ነገሥት 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:27
  • +1ነገ 8:22፤ 2ዜና 4:1

2 ነገሥት 11:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘውዱን።”

  • *

    የአምላክ ሕግ የሰፈረበት ጥቅልል ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:2
  • +ዘፀ 25:21፤ 31:18
  • +1ነገ 1:39, 40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/1991፣ ገጽ 31

2 ነገሥት 11:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 23:12-15

2 ነገሥት 11:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:3
  • +2ዜና 5:12

2 ነገሥት 11:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:4፤ 2ዜና 23:9

2 ነገሥት 11:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:1

2 ነገሥት 11:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 10:25፤ 2ሳሙ 5:3
  • +2ዜና 23:16, 17

2 ነገሥት 11:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:3
  • +ዘዳ 7:25
  • +ዘዳ 13:5
  • +2ዜና 23:18-21

2 ነገሥት 11:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት መጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:4, 15
  • +1ነገ 14:27
  • +2ሳሙ 7:8, 16

2 ነገሥት 11:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:2
  • +2ዜና 24:1

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 11:12ነገ 8:26፤ 11:20፤ 2ዜና 21:5, 6፤ 24:7
2 ነገ. 11:12ነገ 9:27
2 ነገ. 11:12ዜና 21:4፤ 22:10-12
2 ነገ. 11:22ነገ 12:1
2 ነገ. 11:41ነገ 14:27
2 ነገ. 11:42ዜና 23:1-3
2 ነገ. 11:51ነገ 7:1፤ 2ዜና 23:4-7
2 ነገ. 11:92ነገ 11:4
2 ነገ. 11:92ዜና 23:8-11
2 ነገ. 11:111ነገ 14:27
2 ነገ. 11:111ነገ 8:22፤ 2ዜና 4:1
2 ነገ. 11:122ነገ 11:2
2 ነገ. 11:12ዘፀ 25:21፤ 31:18
2 ነገ. 11:121ነገ 1:39, 40
2 ነገ. 11:132ዜና 23:12-15
2 ነገ. 11:142ነገ 23:3
2 ነገ. 11:142ዜና 5:12
2 ነገ. 11:152ነገ 11:4፤ 2ዜና 23:9
2 ነገ. 11:161ነገ 7:1
2 ነገ. 11:171ሳሙ 10:25፤ 2ሳሙ 5:3
2 ነገ. 11:172ዜና 23:16, 17
2 ነገ. 11:18ዘዳ 12:3
2 ነገ. 11:18ዘዳ 7:25
2 ነገ. 11:18ዘዳ 13:5
2 ነገ. 11:182ዜና 23:18-21
2 ነገ. 11:192ነገ 11:4, 15
2 ነገ. 11:191ነገ 14:27
2 ነገ. 11:192ሳሙ 7:8, 16
2 ነገ. 11:212ነገ 11:2
2 ነገ. 11:212ዜና 24:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 11:1-21

ሁለተኛ ነገሥት

11 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ+ ልጇ መሞቱን+ ባየች ጊዜ ተነስታ የንጉሣውያኑን ቤተሰብ* በሙሉ አጠፋች።+ 2 ይሁንና የአካዝያስ እህት የሆነችው የንጉሥ ኢዮራም ልጅ የሆሼባ ሊገደሉ ከነበሩት የንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮዓስን+ ሰርቃ በመውሰድ እሱንና ሞግዚቱን በውስጠኛው መኝታ ክፍል አስቀመጠቻቸው። እነሱም ጎቶልያ እንዳታየው ደብቀው አቆዩት፤ በመሆኑም ሳይገደል ቀረ። 3 እሱም ከእሷ ጋር ለስድስት ዓመት በይሖዋ ቤት ተደብቆ ቆየ፤ በዚህ ጊዜ ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ትገዛ ነበር።

4 በሰባተኛው ዓመት ዮዳሄ መልእክት ልኮ ካራውያን ጠባቂዎቹንና የቤተ መንግሥቱን ዘቦች* የሚያዙትን መቶ አለቆች+ እሱ ወዳለበት ወደ ይሖዋ ቤት አስመጣ። ከዚያም ከእነሱ ጋር ስምምነት* አደረገ፤ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ አስማላቸው፤ ይህን ካደረገም በኋላ የንጉሡን ልጅ አሳያቸው።+ 5 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ ከመካከላችሁ አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት በሰንበት ቀን ገብታችሁ የንጉሡን ቤት*+ በተጠንቀቅ ትጠብቃላችሁ፤ 6 አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት ደግሞ በመሠረት በር ላይ ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ ከቤተ መንግሥቱ ዘቦች ኋላ ባለው በር ላይ ይሆናል። ቤቱን በየተራ ትጠብቃላችሁ። 7 ከመካከላችሁ በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ንጉሡን ከጥቃት ለመከላከል የይሖዋን ቤት በተጠንቀቅ ይጠብቁ። 8 እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ንጉሡን ዙሪያውን ክበቡት። ረድፉን ጥሶ የገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።”

9 መቶ አለቆቹ+ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በሰንበት ቀን ተረኛ የሚሆኑትንና በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑትን የራሳቸውን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።+ 10 ከዚያም ካህኑ በይሖዋ ቤት የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮችና ክብ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። 11 የቤተ መንግሥቱ ዘቦችም+ እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው በስተ ቀኝ በኩል ካለው የቤቱ ጎን አንስቶ በስተ ግራ በኩል እስካለው የቤቱ ጎን ድረስ በመሠዊያውና+ በቤቱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ ቆሙ። 12 ከዚያም ዮዳሄ የንጉሡን ልጅ+ አውጥቶ አክሊሉን* ጫነበት፤ ምሥክሩንም*+ ሰጠው፤ በዚህም መንገድ አነገሡት፤ ደግሞም ቀቡት። እያጨበጨቡም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ይሉ ጀመር።+

13 ጎቶልያ ሕዝቡ ሲሯሯጥ ስትሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ቤት ወዳለው ሕዝብ መጣች።+ 14 ከዚያም በነበረው ልማድ መሠረት ንጉሡ ዓምዱ አጠገብ ቆሞ አየች።+ አለቆቹና መለከት ነፊዎቹ+ ከንጉሡ ጋር ነበሩ፤ የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ እጅግ እየተደሰተና መለከት እየነፋ ነበር። በዚህ ጊዜ ጎቶልያ ልብሷን ቀዳ “ይህ ሴራ ነው! ሴራ ነው!” በማለት ጮኸች። 15 ካህኑ ዮዳሄ ግን በሠራዊቱ ላይ የተሾሙትን መቶ አለቆች+ “ከረድፉ መካከል አውጧት፤ እሷን ተከትሎ የሚመጣ ሰው ካለ በሰይፍ ግደሉት!” በማለት አዘዛቸው። ካህኑ “በይሖዋ ቤት ውስጥ እንዳትገድሏት” ብሎ ነበር። 16 በመሆኑም ያዟት፤ ፈረሶች ወደ ንጉሡ ቤት*+ የሚገቡበት ቦታ ላይ ስትደርስ ተገደለች።

17 ከዚያም ዮዳሄ የይሖዋ ሕዝብ ሆነው እንዲቀጥሉ ይሖዋ፣ ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ፤+ በተጨማሪም ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ።+ 18 ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ወደ ባአል ቤት* መጥቶ መሠዊያዎቹን አፈራረሰ፤+ ምስሎቹንም እንክትክት አድርጎ ሰባበረ፤+ የባአል ካህን የነበረውን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት።+

ከዚያም ካህኑ በይሖዋ ቤት ላይ የበላይ ተመልካቾችን ሾመ።+ 19 በተጨማሪም ንጉሡን አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች እንዲያመጡት መቶ አለቆቹን፣+ ካራውያን ጠባቂዎቹን፣ የቤተ መንግሥት ዘቦቹንና+ የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ እነሱም ወደ ቤተ መንግሥቱ ዘቦች በር በሚወስደው መንገድ በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ።* እሱም በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ተቀመጠ።+ 20 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በንጉሡ ቤት በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት።

21 ኢዮዓስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ