የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ከገጸ ኅብስቱ በላ (1-9)

      • ዳዊት አእምሮው እንደተነካ ሰው ሆነ (10-15)

1 ሳሙኤል 21:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 22:9, 19
  • +1ሳሙ 18:13

1 ሳሙኤል 21:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የፆታ ግንኙነት ከመፈጸም ተቆጥበው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:15፤ ዘሌ 15:16፤ 2ሳሙ 11:11
  • +ዘፀ 25:30፤ ዘሌ 24:5, 9፤ ማቴ 12:3, 4

1 ሳሙኤል 21:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 15:18

1 ሳሙኤል 21:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 24:7-9፤ ማር 2:25, 26፤ ሉቃስ 6:3, 4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 76

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2005፣ ገጽ 30

    9/1/2002፣ ገጽ 18

1 ሳሙኤል 21:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 22:9፤ መዝ 52:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
  • +ዘፍ 36:1

1 ሳሙኤል 21:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 17:2, 50
  • +1ሳሙ 17:51, 54
  • +ዘፀ 28:6

1 ሳሙኤል 21:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 27:1
  • +ኢያሱ 11:22፤ 1ሳሙ 5:8፤ 17:4፤ 27:2፤ መዝ 56:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ

1 ሳሙኤል 21:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:6-8፤ 29:4, 5

1 ሳሙኤል 21:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 56:3, 6

1 ሳሙኤል 21:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጃቸውም ላይ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2024፣ ገጽ 2

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2005፣ ገጽ 24

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ሳሙ. 21:11ሳሙ 22:9, 19
1 ሳሙ. 21:11ሳሙ 18:13
1 ሳሙ. 21:4ዘፀ 19:15፤ ዘሌ 15:16፤ 2ሳሙ 11:11
1 ሳሙ. 21:4ዘፀ 25:30፤ ዘሌ 24:5, 9፤ ማቴ 12:3, 4
1 ሳሙ. 21:5ዘሌ 15:18
1 ሳሙ. 21:6ዘሌ 24:7-9፤ ማር 2:25, 26፤ ሉቃስ 6:3, 4
1 ሳሙ. 21:71ሳሙ 22:9፤ መዝ 52:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
1 ሳሙ. 21:7ዘፍ 36:1
1 ሳሙ. 21:91ሳሙ 17:2, 50
1 ሳሙ. 21:91ሳሙ 17:51, 54
1 ሳሙ. 21:9ዘፀ 28:6
1 ሳሙ. 21:101ሳሙ 27:1
1 ሳሙ. 21:10ኢያሱ 11:22፤ 1ሳሙ 5:8፤ 17:4፤ 27:2፤ መዝ 56:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
1 ሳሙ. 21:111ሳሙ 18:6-8፤ 29:4, 5
1 ሳሙ. 21:12መዝ 56:3, 6
1 ሳሙ. 21:13መዝ 34:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ሳሙኤል 21:1-15

አንደኛ ሳሙኤል

21 በኋላም ዳዊት ካህኑ አሂሜሌክ ወደሚገኝበት ወደ ኖብ+ መጣ። አሂሜሌክም ዳዊትን ሲያገኘው ተንቀጠቀጠ፤ እሱም “ምነው ብቻህን? ሰው አብሮህ የለም?” አለው።+ 2 ዳዊትም ለካህኑ ለአሂሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ንጉሡ አንድ ጉዳይ እንዳስፈጽም አዞኝ ነበር፤ ሆኖም ‘ስለሰጠሁህ ተልእኮና ስላዘዝኩህ ነገር ማንም ሰው ምንም ነገር እንዳያውቅ’ ብሎኛል። ከሰዎቼም ጋር የሆነ ቦታ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረናል። 3 ስለዚህ አሁን እጅህ ላይ አምስት ዳቦ ካለ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።” 4 ካህኑ ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ማንኛውም ሰው የሚበላው ዓይነት ዳቦ የለኝም፤ ሰሞኑን ሰዎቹ ራሳቸውን ከሴት ጠብቀው*+ ከሆነ ግን የተቀደሰው ኅብስት አለ።”+ 5 ስለዚህ ዳዊት ካህኑን እንዲህ አለው፦ “ከዚህ በፊት ለውጊያ እንደወጣሁባቸው ጊዜያት ሁሉ አሁንም ፈጽሞ ሴቶች ወደ እኛ አልቀረቡም።+ ተራ በሆነ ተልእኮም እንኳ የሰዎቹ አካል ቅዱስ ከነበረ ታዲያ ዛሬማ እንዴት ይበልጥ ቅዱስ አይሆን!” 6 በመሆኑም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው፤+ ምክንያቱም ትኩስ ኅብስት በሚተካበት ቀን ከይሖዋ ፊት ከተነሳው ገጸ ኅብስት በስተቀር ሌላ ዳቦ አልነበረም።

7 ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በይሖዋ ፊት እንዲቆይ በመገደዱ ያን ቀን እዚያ ነበር። ዶይቅ+ የተባለው ይህ ኤዶማዊ+ የሳኦል እረኞች አለቃ ነበር።

8 ከዚያም ዳዊት አሂሜሌክን “ንጉሡ የሰጠኝ ተልእኮ አስቸኳይ ስለነበር ሰይፌንም ሆነ የጦር መሣሪያዎቼን አልያዝኩም፤ እዚህ አንተ ጋ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖራል?” አለው። 9 ካህኑም “በኤላህ ሸለቆ*+ አንተ የገደልከው የፍልስጤማዊው የጎልያድ ሰይፍ+ አለ፤ ያውልህ ከኤፉዱ+ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሎ ተቀምጧል። ከእሱ ሌላ እዚህ ምንም ስለሌለ ከፈለግክ እሱን ውሰደው” አለው። ዳዊትም “ከእሱ የተሻለማ የትም አይገኝም። እሱኑ ስጠኝ” አለው።

10 በዚያም ቀን ዳዊት ተነስቶ ከሳኦል ሸሸ፤+ ከጊዜ በኋላም ወደ ጌት+ ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ። 11 የአንኩስ አገልጋዮችም እንዲህ አሉት፦ “ይህ የምድሪቱ ንጉሥ፣ ዳዊት አይደለም?

‘ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤

ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ’+

በማለት እየዘፈኑ የጨፈሩለትስ ለዚህ ሰው አይደለም?” 12 ዳዊትም ይህን ቃል በቁም ነገር ተመለከተው፤ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።+ 13 በመሆኑም በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ፤+ በመካከላቸውም* እንደአበደ ሰው አደረገው። የከተማዋን በሮች ይቦጫጭር እንዲሁም ለሃጩን በጢሙ ላይ ያዝረበርብ ጀመር። 14 አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ተመልከቱ፣ ሰውየው እኮ እብድ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው? 15 ይህን ሰው ፊቴ እንዲህ እንዲያብድ ያመጣችሁት እኔ እብድ አጥቼ ነው? ይህስ ሰው ቤቴ መግባት ይገባዋል?”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ