የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 10/8 ገጽ 16
  • ሲጋራ ማጨስ ለማቆም የሚረዱ አሥር ዘዴዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሲጋራ ማጨስ ለማቆም የሚረዱ አሥር ዘዴዎች
  • ንቁ!—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሲጋራ ማቆም የሚኖርብህ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2000
  • መሰናክሎቹን ለማለፍ ዝግጁ ሁን
    ንቁ!—2010
  • ማጨስ በአምላክ ዘንድ እንዴት ይታያል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ማጨስ እና ክርስቲያናዊ አመለካከት
    ንቁ!—1994
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1994
g94 10/8 ገጽ 16

ሲጋራ ማጨስ ለማቆም የሚረዱ አሥር ዘዴዎች

1.ማጨስ ለማቆም ከልብ መነሳሳት። ማጨስ ለማቆም የሚገፋፋ እርግጠኛ ምክንያት ይኑርዎት። ለራስዎ ጥሩ ግምት እንዲኖርዎት መፈለግ፣ የአሁንም ሆነ የወደፊት ጤንነትዎ፣ አደገኛ በሆነው ልማድዎ ለሚነኩ ቤተሰቦችዎ ያለዎት አሳቢነት፣ በአካልም ሆነ በሥነ ምግባር በራስዎና በአምላክ ፊት ንጹሕ ሆኖ ለመገኘት ያለዎት ፍላጎት ማጨስ ለማቆም የሚያነሳሱ ምክንያቶች ናቸው።

2.የሚያቆሙበትን ቁርጥ ያለ ቀን ይወስኑና ውሳኔዎን አክብረው ይገኙ። በአንድ ጊዜ ያቁሙ። ብዙ የሚያስቸግርዎት ቢሆንም ፈጣን ፈውስ የሚያስገኝልዎት ይህ ዘዴ ነው።

3.ልማዱን ለማሸነፍ አንዳንድ ቆራጥ እርምጃዎችን ይውሰዱ። እቤትዎ ያሉትን ሲጋራዎች በሙሉ ሰባብረው ውኃ ይድፉባቸው። የትንባሆ ሽታ ያላቸውን ልብሶችዎን በሙሉ ያሳጥቡ። አዲስና ንጹሕ መሆን ይጀምሩ። አዲስና ንጹሕ እንደሆኑም ይሰማዎ!

4.ሙሉ በሙሉ ከኒኮቲን እስኪላቀቁ ድረስ በትንባሆ የታፈኑ አካባቢዎችንና የሚያጨሱ ጓደኞችን ይራቁ። ማጨስ የሚከለከልባቸውን እንደ ቤተ መዘክርና ቤተ መጻሕፍት የመሰሉትን ቦታዎች ይጎብኙ።

5.ለትንባሆ ያጠፉ የነበረውን ገንዘብ አጠራቅመው ከአንድ ወር በኋላ ይቁጠሩት! በጣም የሚያስፈልግዎትን ነገር ይግዙበት። አለበለዚያም በድል አድራጊነትዎ ደስ ሊለው ለሚችል ወዳጅዎ አንድ ዓይነት ስጦታ ይግዙበት።

6.ሲጋራ በሚያጨሱባቸው የተለመዱ ጊዜያት ጣቶችዎ ሥራ እንዳይፈቱ አንድ ዓይነት ነገር ይስሩባቸው። ማጨስ ሲያምርዎት ማስቲካ (የኒኮቲን ማስቲካ መሆን የለበትም) ያኝኩ ወይም ሜንታ ከረሜላ ይምጠጡ። ከምግብ በኋላ ሲጋራ ከማጨስ ይልቅ ጥርስዎን ያጽዱ። በእግር ይንሸራሸሩ፣ ደብዳቤ ይጻፉ፣ ስፌት ይስፉ፣ በአትክልት ቦታዎ ይሥሩ፣ አንዳንድ ነገሮችን ይጠግኑ፣ መኪናዎን ያጽዱ ወዘተ።

7.ጭንቀት ወይም ውጥረት ሲሰማዎ በቀስታና በረዥሙ ይተንፍሱ። እጅዎን ወደ ሲጋራ ከመስደድ ይልቅ ብዙ ውኃና የፍራፍሬ ጭማቂ ይጠጡ። ፈሳሽ ነገሮች የውስጥ አካላትን ያጸዳሉ።

8.አቅምዎ በፈቀደ መጠን አካላዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ። ምን ያህል እንቅስቃሴ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ከሐኪምዎ ጋር በቅድሚያ ይማከሩ። የአካላዊ ብቃትዎ መሻሻል ያበረታታዎታል።

9.አልኮል የማጨስ ፍላጎትዎን ሊያነሳሳ ስለሚችል ይወስዱ የነበረውን የአልኮል መጠን ይቀንሱ። አልኮልና ሲጋራ “እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ።” መጠጥ የሚጠጣባቸውን ማኅበራዊ ግንኙነቶች ያቋርጡ። የትንባሆ ማስታወቂያዎችን በከፍተኛ ጥርጣሬ ይመልከቱ። ውሸታቸውንና ግብዝነታቸውን ያጢኑ። ዳግመኛ እንዳይሸነፉ ይጠንቀቁ።

10.የይሖዋ ምሥክር ለመሆን በማሰብ ላይ ከሆኑ አምላክ እንዲረዳዎት ከልብ ይጸልዩ። ከጸሎትዎ ጋር የሚስማማ እርምጃም ይውሰዱ። ተአምር ይፈጠራል ብለው አይጠብቁ። የራስዎ ጥረት አስፈላጊ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ