የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 7/8 ገጽ 32
  • አንድ መነኩሴ እውነትን አወቀ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንድ መነኩሴ እውነትን አወቀ
  • ንቁ!—1994
ንቁ!—1994
g94 7/8 ገጽ 32

አንድ መነኩሴ እውነትን አወቀ

ሉዊ ፐርኖ የሚባል በጅቡቲ የሚኖር አንድ ካቶሊክ መነኩሴ ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት የተባለውን መጽሐፍ ከአንድ የይሖዋ ምሥክር አገኘ። የአንድ ካቶሊክ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የነበረው ሉዊ ሃይማኖቱ ወጣቶችን በሚያጋጥሟቸው ችግሮች ሊረዳቸው የሚችል ግልጽ ትምህርት ለምን እንደማይሰጥ ይገርመው ነበር።

ሉዊ በዚያው ምሽት መጽሐፉን ማንበብ ይጀምራል። በመጽሐፉ በጣም ተመስጦ ስለነበረ ሳይጨርስ ሊያስቀምጠው አልቻለም። እውነተኛው ሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ሳይበርዝና ሳይከልስ ለሰዎች ጠንካራ መሠረት ያለው መመሪያ መስጠት ይኖርበታል ብሎ ያምን ነበር። አሁን ይህን የሚያሟላ መጽሐፍ አገኘ።

በሚቀጥለው ቀን ሉዊ መጽሐፉን ለሰጠው ምሥክር እውነትን እንዳገኘ ነገረው። በዚያው ሳምንት ራሱን ከምንኩስና ብቻ ሳይሆን ከካቶሊክነት አሰናበተ። የይሖዋ ምሥክር ከሆነ በኋላ የተማራቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ለሌሎች ሰዎች ማስተማር ጀመረ።

የይሖዋ ምሥክሮች ድርጅት ሰዎች ስለ አምላክ ዓላማዎች እንዲያውቁ ለመርዳት ራሳቸውን የወሰኑ ከአራት ሚልዮን የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የሚገኙበት ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ብንሰጥዎ ደስ የሚልዎት ከሆነ ወይም አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርዎት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 2 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ