የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 5/8 ገጽ 17-18
  • መሃይምነት በመላው ዓለም የሚገኝ ችግር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መሃይምነት በመላው ዓለም የሚገኝ ችግር
  • ንቁ!—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ሕዝቦችና የማንበብና የመጻፍ ችሎታ
    ንቁ!—1998
  • መሃይማንን እንዲያነቡ መርዳት
    ንቁ!—1998
  • በቃል ከሚተላለፉ መልእክቶች ወደ ቅዱሳን መጻሕፍት ጽሕፈትና የጥንቶቹ ክርስቲያኖች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1998
g98 5/8 ገጽ 17-18

መሃይምነት በመላው ዓለም የሚገኝ ችግር

በናይጄርያ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

አልማዝ የምትኖረው በኢትዮጵያ ነው። ልጅዋን አመማትና ሐኪም አንድ ብልቃጥ መድኃኒት አዘዘላት። አልማዝ ግን ማንበብ ስለማትችል መድኃኒቱ ምን ያህል፣ መቼና እንዴት እንደሚወሰድ ማወቅ አልቻለችም። እንደ አጋጣሚ ማንበብ የሚችል ጎረቤት ነበራት። ከዚያም መድኃኒቱን እንደሚገባ ሰጠቻትና ልጅዋ ዳነች።

ራሙ በሕንድ አገር የሚኖር ገበሬ ነው። ልጁ የምታገባበት ጊዜ ሲደርስ መሬቱን በዋስትና አስይዞ ከመንደሩ አበዳሪዎች ገንዘብ ለመበደር ወሰነ። ማንበብም ሆነ መጻፍ ስለማይችል ምን እንደሚል በማያውቀው ሰነድ ላይ በጣቱ አሻራ ፈረመ። ከጥቂት ወራት በኋላ ራሙ የፈረመው ሰነድ የሽያጭ ውል መሆኑን አወቀ። አሁን መሬቱ የሌላ ሰው ሆኗል።

ማይክል በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ በአንድ ሰፊ እርሻ ላይ ይሠራል። የቅርብ አለቃው ለከብቶች የመኖ ማሟያ የሆነ አልሚ ምግብ እንዲሰጥ አዘዘው። ማይክል እላያቸው ላይ ጽሕፈት ያለባቸው ሁለት ጆንያዎች አገኘ። ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ማንበብ ስለማይችል ትክክል ያልሆነውን ጆንያ መረጠ። ከበርካታ ቀናት በኋላ ከብቶቹ ሞቱ። ማይክል እንዲመገቡ የሰጣቸው መርዝ ነበር። ወዲያው ከሥራ ተባረረ።

ማይክል መጻፍና ማንበብ የማይችል መሃይም በመሆኑ ምክንያት ከሥራ ተባረረ። አሠሪው ደግሞ ለእርድ የደረሱ የደለቡ ከብቶቹን አጣ። ራሙ መሃይም በመሆኑ ምክንያት መሬቱን ተነጠቀ። አልማዝም ልጅዋን በሞት ልታጣ ትችል ነበር።

በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት) ግምት መሠረት አካለ መጠን ከደረሱ የዓለም ሕዝቦች መካከል ከአንድ አራተኛ ማለትም ከ960 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ማንበብም ሆነ መጻፍ አይችሉም።a በታዳጊ አገሮች ለአካለ መጠን ከደረሱ ከሦስት ሰዎች መካከል አንዱ መሃይም ነው። እነዚህ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ አልማዝ፣ ራሙና ማይክል በመንገድ ላይ የሚተከሉ ምልክቶችን፣ ጋዜጦችን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አንብበው መረዳት አይችሉም። በመጽሔቶችና በመጻሕፍት ውስጥ ከተከማቸው ተዝቆ የማያልቅ የእውቀት ጎተራ የመቋደስ ዕድል ተነፍጓቸዋል። ደብዳቤ ለመጻፍ ወይም ቀላል ቅጾች እንኳ ለመሙላት አይችሉም። እንዲያውም አብዛኞቹ ስማቸውን እንኳን ጽፈው መፈረም አይችሉም። መሠረታዊ የሆነ የማንበብና የመጻፍ ችሎታ በሚጠይቁ ሥራዎች መወዳደር ስለማይችሉ ሥራ አጥ ሆነው ይኖራሉ፤ እንዲሁም ችሎታቸውና ክህሎታቸው ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

ይህ አኃዝ መሠረታዊ የሆነ የማንበብና የመጻፍ ችሎታ ቢኖራቸውም የዕለት ተዕለት ኑሯቸው በሚፈልግባቸው መጠን አጣርተው ማንበብ ወይም መጻፍ የማይችሉትን በርካታ ሰዎችን አይጨምርም። እንደነዚህ ያሉት መሃይማን በዩናይትድ ስቴትስ ብቻ 27 ሚልዮን ይደርሳሉ።

ልጆችስ? በሁሉም አገሮች ጥናት ባለመደረጉ ምክንያት ትክክለኛውን አሐዝ ለማወቅ ባይቻልም የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት በመላው ዓለም 100 ሚልዮን የሚሆኑ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ትምህርት ቤት የመግባት ዕድል አያገኙም። ሌሎች 100 ሚልዮን የሚያክሉ ልጆች ደግሞ ከመሠረተ ትምህርት ደረጃ እልፍ አይሉም። እንዲያውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕዝባዊ መረጃ ክፍል እንደሚለው በታዳጊ አገሮች ባሉ የገጠር አካባቢዎች ከአራተኛ ክፍል በላይ የመማር ዕድል የሚያገኙት ልጆች ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። በኢንዱስትሪ በበለጸጉ አገሮች ደግሞ ብዙ ልጆች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ ይልቅ ቴሌቪዥን በመመልከት የሚያሳልፉት ጊዜ ይበልጣል።

አብዛኛውን ጊዜ መሃይም ልጆች ካደጉም በኋላ ከመሃይምነት አይላቀቁም። ለዚህ ዓለም አቀፋዊ ችግር አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው? ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ጎልማሳ ሰዎችን ለመርዳት ምን ማድረግ ይቻላል? በሚቀጥለው ርዕስ እነዚህን ጥያቄዎች እንመረምራለን።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ዩኔስኮ በሚሰጠው ፍቺ መሠረት መሃይም የሚባለው 15 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ዕድሜ ኖሮት ሕይወቱን የሚመለከቱ ቀላልና አጭር የሆኑ መግለጫዎችን አንብቦ ለመረዳት ወይም ለመጻፍ የማይችል ሰው ነው።

[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ለአካለ መጠን ከደረሱ የዓለም ሕዝቦች መካከል ከአንድ አራተኛ የሚበልጡት ማንበብም ሆነ መጻፍ አይችሉም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ