የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g96 1/8 ገጽ 32
  • “ማጨስ ጸያፍ ልማድ ነው”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ማጨስ ጸያፍ ልማድ ነው”
  • ንቁ!—1996
ንቁ!—1996
g96 1/8 ገጽ 32

“ማጨስ ጸያፍ ልማድ ነው”

በቅርብ ዓመታት የካሊፎርንያ የጤና አገልግሎት ቢሮ በማጨስ ላይ ቆራጥነት የተሞላበት የትምህርት ዘመቻ አካሂዶ ነበር። መልእክቱ አጭርና ቀጥተኛ ሲሆን በመላው ካሊፎርንያ ውስጥ በሚገኙ የንግድ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ ነበር። አንዳንዶቹ መልእክቶች ምንድን ናቸው? “አጫሾች ሱሰኞች ናቸው። ትንባሆ አምራች ድርጅቶች ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ናቸው። ማጨስ ጸያፍ ልማድ ነው።” “በዚህ ዓመት 50,000 የሚያህሉ የማያጨሱ ሰዎች ከአጫሾች የሚወጣውን ጭስ በመተንፈሳቸው ምክንያት ይሞታሉ። ማጨስ ጸያፍ ልማድ ነው።” በአንድ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሲጋራ ፓኬት ሥር የተለጠፈ ሌላ መልእክት “አሁን ግዛ። ሌላ ጊዜ ትከፍላለህ” ይላል። የምትከፍለው ግን ሕይወትህን ነው። አንድ በስፓንኛ የተጻፈ ቅስት “ሚ ምዌሮ ፓር ፉማር” ይላል። “አጭሼ ልሙት” የሚል ትርጉም ያለው የምጸት አነጋገር ነው። በከፊል የራስ ቅልና በከፊል የሰው ፊት የተሳለበት ሥዕል መልእክቱን ይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል።

የጤና ቢሮው ሰዎች ከትንባሆና ከኒኮቲን እንዲርቁ ለመምከር የተጠቀመበት ሌላው ዘዴ “ሞት” የተባለ የንግድ ስም የተሰጠው ሲጋራ ማውጣት ነው። ጥቁሩ የሲጋራ ፓኬት የራስ ቅልና የኤክስ ቅርጽ ያላቸው አጥንቶች ያሉበት ሲሆን “ሲጋራ ሱስ የሚያስይዝና ሰውነትን የሚያመነምን ነገር ነው። የማታጨስ ከሆነ አትጀምር። የምታጨስ ከሆንክ አቁም” የሚል መልእክት ሰፍሮበታል።

በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ የተለጠፉት አስደንጋጭ መልእክቶች ቀደም ሲል አጫሾች በነበሩ ሰዎች ላይ ስላስከተሉት ውጤት በትክክል ለማወቅ ያዳግታል። ሆኖም ባለፉት ስድስት ዓመታት “በካሊፎርንያ የሲጋራ ፍጆታ በ27 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህ በመላው አሜሪካ ከተገኘው አማካይ ቅናሽ በሦስት እጥፍ ይበልጣል።” (ዘ ዋሽንግተን ፖስት ናሽናል ዊክሊ ኤድሽን) እንዲያውም ይህ የፖስተር ዘመቻ ወደፊት ማጨስ ሊጀምሩ የሚችሉ ሰዎችን ከዚህ አደገኛ ልማድ ሳይጠብቃቸው አልቀረም። በእርግጥም ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ከዚህ ንጹሕ ያልሆነና በራስ ወዳድነት ላይ የተመሠረተ ተግባር መራቅ ይኖርባቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ “ወዳጆች ሆይ፣ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፣ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ” በማለት ጽፏል።— 2 ቆሮንቶስ 7:1

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ