የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 2/8 ገጽ 14
  • እጅን ታጥቦ ማድረቅ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እጅን ታጥቦ ማድረቅ!
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጤንነትህን ማሻሻል የምትችልባቸው መንገዶች
    ንቁ!—2015
  • 2. ንጽሕናውን ጠብቁ
    ንቁ!—2012
  • ጤንነትህን ለመጠበቅ የሚረዱ ስድስት መንገዶች
    ንቁ!—2003
  • ታላቁ ሰው ትሕትና የሚጠይቅ አገልግሎት ሰጠ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 2/8 ገጽ 14

እጅን ታጥቦ ማድረቅ!

በጉንፋንና በሌሎች በሽታዎች የምንለከፈው እንዴት ነው? በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያና የወረርሽኝ ጥናት ባለ ሙያዎች ማኅበር እንደገለጸው ከእነዚህ በሽታዎች መካከል ቢያንስ 80 በመቶ የሚሆኑት ከአንዱ ወደ ሌላው የሚተላለፉት በአየር ሳይሆን በእጆቻችን ነው። በመሆኑም እጅ መታጠብ በሽታ እንዳይዛመት ለመግታት ከሚያስችሉት ዘዴዎች መካከል ከሁሉ የተሻለና ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ይታመናል። ሆኖም ብዙዎች ከተጸዳዱ ወይም ከተናፈጡ በኋላ ወይም ምግብ ከመንካታቸው በፊት እጃቸውን የሚታጠቡት ሁልጊዜ አይደለም። እርግጥ ነው በርካታ ሰዎች በእነዚህ ወቅቶች ሁልጊዜ እጃቸውን ይታጠባሉ። ይሁን እንጂ በጥድፊያና እንዲያው ለይስሙላ ብቻ እጅ ላይ ውኃ በማፍሰስ እጅን መታጠብ በበሽታ የመለከፉን አጋጣሚ አይቀንሰውም።

እጅን በተገቢው መንገድ ማድረቅም እጅን ከመታጠብ ያላነሰ ጠቀሜታ አለው። እንግሊዝ አገር በሚገኘው በዌስትሚንስቴር ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩ ተመራማሪዎች እንደደረሱበት በርካታ ሰዎች በተለይ ደግሞ ሙቅ አየር በሚሰጥ የእጅ ማድረቂያ የሚጠቀሙ ሰዎች ከታጠቡ በኋላ እጃቸውን በሚገባ አያደርቁም። ብዙዎቹ የቀረውን የሚያደርቁት ልብሳቸው ላይ እጃቸውን በመጥረግ ነው። ይህ ደግሞ በእጅ ላይ የሚቀሩት በጣም አደገኛ ረቂቅ ሕዋሳት እንዲዛመቱ በር ይከፍታል። አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ በሚውሉ የወረቀት ፎጣዎች ወይም ሌላ ሰው ባልተጠቀመባቸው ንጹሕ የጨርቅ ፎጣዎች ተጠቅሞ እጅን ሙሉ በሙሉ ማድረቅ ከሁሉ የተሻለ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እጅን ስለ መታጠብ የሚከተሉትን ምክሮች ይለግሳል:-

• ሁልጊዜ ሞቅ ባለ በሚንቆረቆር ውኃና በሳሙና ተጠቀሙ። የሚንቆረቆረቆር ውኃ ማግኘት የማትችሉና በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ በተጠራቀመ ውኃ የምትጠቀሙ ከሆነ በዕቃው በተጠቀማችሁበት ቁጥር በጀርም መግደያ መርዝ አጽዱት። እርጥብ ፎጣዎች አጥጋቢ በሆነ መንገድ እጅን አያነጹም።

• የሳሙናው አረፋ እስኪወጣ ድረስ እጆቻችሁን ስበቁት፤ ቢያንስ ለ15 ሰኮንድ ያህል እንደዚያ አድርጉ። የእጆቻችሁን መዳፍና ውጭውን ጨምሮ በጣቶቻችሁ መካከል ያለውን ቦታ እንዲሁም የጥፍሮቻችሁን ውስጠኛ ክፍል በደንብ አጽዱ።

• ሞቅ ባለ የቧንቧ ውኃ እጃችሁን አለቅልቁ።

• አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ በሚውል ወይም ሌላ ማንም ሰው ባልተጠቀመበት ፎጣ ተጠቅማችሁ እጃችሁን አድርቁ። ንጹህ በሆነው እጃችሁ የቧንቧውን መዝጊያው ወይም የፎጣ ማንጠልጠያውን አትንኩ።

• እጃችሁን እንዳይነካ ለመከላከል እንድትችሉ ቧንቧውን በፎጣው ይዛችሁ ዝጉት።

• ልጆች በቧንቧ ውኃ ሲታጠቡ ቆመው እጃቸውን ምንም ነገር ሳይደገፉ ሊታጠቡ በሚችሉበት ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ልጆች ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች እንዲከተሉ ከረዳችኋቸው በኋላ እናንተ ራሳችሁ እጃችሁን ታጠቡ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ