የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 1/8 ገጽ 32
  • ሰፊ ተቀባይነት አለው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሰፊ ተቀባይነት አለው
  • ንቁ!—1999
ንቁ!—1999
g99 1/8 ገጽ 32

ሰፊ ተቀባይነት አለው

“አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በሚል ርዕስ ያሳተማችሁት ብሮሹር በጣም ደስ የሚል ነበር። ዕድሜዬ ገና አሥር ዓመት ቢሆንም ትምህርቱን ለመረዳት አልተቸገርኩም፤ ለማንበብም ቀላል ነበር። ሐሳቡን በሚገባ ተረድቼዋለሁ፤ ብሮሹሩን በጣም ወድጄው ስለነበር ትምህርት 16 ላይ ስደርስ እንዳያልቅብኝ ስል ላነብበው አልፈለግሁም ነበር። ምነው ባላለቀ ብዬ አስቤ ነበር።”

እዚህ ላይ ሽፋኑን የምትመለከቱት ብሮሹር ለልጆች ታስቦ የተዘጋጀ አልነበረም። ሆኖም ትምህርቱ ግልጽና ቀላል በሆነ መንገድ የቀረበ በመሆኑ ልጆች እንኳን የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ትምህርቶችና አምላክ ከእኛ የሚፈልገውን የአኗኗር ዓይነት ሊረዱ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ብሮሹሩ እንደሚከተለው ላሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- መዋሸትን እንዴት ልንመለከተው ይገባል? ቁማር መጫወት ተገቢ ነው? መስከር ስህተት ነው? ባልተጋቡ ሰዎች መካከል ወሲብ መፈጸም ተገቢ ነው?

እርስዎም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደ ሆነው ይጻፉ። አሥራ ስድስቱ ትምህርቶች መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት በሚያስችል መንገድ የተዘጋጁ ናቸው። አንዳንዶቹ ትምህርቶች “አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?፣” “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?፣” “አምላክን የሚያስደስት የቤተሰብ ሕይወት፣” እና “አምላክ የሚጠላቸው ድርጊቶች” የሚል ርዕስ አላቸው።

□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተሰኘውን ብሮሹር ላኩልኝ።

መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ የሚያስጠናኝ ሰው እፈልጋለሁ።

□ ስም_አድራሻ_ከተማ_አገር_

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ