የሰውየውን ገንዘብ አዳነለት
በምዕራብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ ውስጥ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ በታክሲ ይጓዝ የነበረ ሰው አብሮት የተሳፈረውን ሰው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ውስጥ በሚገኘው “አምላክ የማይደሰትባቸው ልማዶች” በሚለው ትምህርት ያወያየዋል። ታክሲው አንድ ምግብ ቤት አጠገብ ደርሶ ሲቆም በብሮሹሩ የተማረከው ይህ ሰው ወደ ያዘው ጥቅልል እያመለከተ “ይህ ገንዘብ ነው። ... ከታክሲው ጀርባ ተጭነው ከነበሩት ሻንጣዎች መካከል ሰርቄው ነው” አለ።
ይሁን እንጂ ገንዘቡን የወሰደው ሰው ባደረገው ነገር በመጸጸቱ ገንዘቡን ለባለቤቱ ለመመለስ ፈልጎ ነበር። አብሯቸው ይጓዝ የነበረ አንድ ወጣት ነጋዴ ጥቅልሉ የእሱ መሆኑን ተናገረ። በጥቅልሉ ውስጥ 150,000 ናይራ (ወደ 1,700 የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ) ይገኝ ነበር። ሊሰርቀው የፈለገውን ሰው 500 ኪሎ ሜትር ያክል ተከታትሎ የመጣው ይህ ሌባ በብሮሹሩ ላይ የሚገኘውን እውቀት ለእሱ ያካፈለውን ሰው ማመስገን እንዳለበት ለነጋዴው ነገረው። ገንዘቡን እንዲመልስ ያደረገው ይህ እውቀት መሆኑን ገለጸ።
የታክሲው ሹፌርና ሌሎች ተሳፋሪዎች የሆነውን ነገር ሲያውቁ በጣም ተገረሙ፤ ሁሉም ብሮሹሩን ለማግኘት እንደሚፈልጉ ተናገሩ። ነጋዴው ከዚያ ቀደም የይሖዋ ምሥክሮች እንዲያነጋግሩት በፍጹም ፈቃደኛ አልነበረም። አሁን ግን መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት እንደሚፈልግ ገልጿል።
እርስዎም ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ጠቃሚ የሆነ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።