ገጽ ሁለት
የአካል ጉዳተኞች ያላቸው ተስፋ 3-10
በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እግራቸውን ወይም እጃቸውን ያጣሉ። ለእንዲህ ዓይነቱ አደጋ ሊያጋልጡህ ከሚችሉት ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? የአካል ጉዳተኞች አስደሳችና ፍሬያማ የሆነ ሕይወት መምራት ይችላሉ?
በአምላክ ፊት ዋጋ አላችሁ! 15
ምንም ዋጋ የለኝም የሚል ስሜት ተፈታትኖህ ያውቃል? ፈጣሪያችን ለአንተ ያለውን አመለካከት ማወቅህ በእጅጉ ሊያጽናናህ ይችላል።
የአስቤስቶስ ታሪክ—ከሕይወት መድህንነት ወደ ሞት ጥላነት 22
አስቤስቶስ በግንባታው ኢንዱስትሪ ላይ ከአንዴም ሁለቴ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል:- መጀመሪያ ወደ ግንባታው ዓለም ሲገባ፤ በኋላ ደግሞ ከግንባታው ዓለም ሲወጣ።