መጽሐፍ ቅዱስን በድጋሚ እንዲያነብ አበረታቶታል
በሜክሲኮ የሚኖርን አንድ ሰው እንዲህ እንዲያደርግ የረዳው ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለው ብሮሹር ነው። ብሮሹሩን በተመለከተ እንዲህ ሲል ጽፏል:-
“ርዕሰ ጉዳዮቹ የቀረቡበት አዲስና ምክንያታዊ መንገድ አንባቢው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነብ ፍላጎት ያሳድርበታል። ... እኔ በበኩሌ መግቢያውን፣ ማጣቀሻዎቹን፣ እንዲሁም ‘በሕይወት በሚገኙ ቋንቋዎች “የሚናገር” መጽሐፍ፣’ ‘ይህ መጽሐፍ እምነት ሊጣልበት የሚችል ነውን?’ እና ‘ይህ መጽሐፍ ከሳይንስ ጋር ይስማማልን?’ የሚሉትን ርዕሶች አስደሳች ሆነው አግኝቼያቸዋለሁ። እያንዳንዱ ርዕስ ቀላል፣ አሳማኝ መሠረት ያለውና ግልጽ ማብራሪያና መግለጫ የተሰጠበት ነው። ...
“በግሌ በውስጡ ከቀረበው ትምህርት ከፍተኛ ማበረታቻ አግኝቻለሁ። ከዚህ ቀደም መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከ ዳር በማንበብ ደስታ አግኝቼ ነበር። ሆኖም ይህን ብሮሹር ካነበብኩ በኋላ ያደረግሁት የመጀመሪያ ነገር በትላልቅ ፊደላት የተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት ነበር። አሁን መጽሐፉን ካገኘሁ ከአንድ ሳምንት በኋላ ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ የማወቅ ፍላጎት አድሮብኝ መጽሐፍ ቅዱስን በጋለ ስሜት እያነበብኩ ነው።”
እርስዎም ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ይህን ግሩም የሆነ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያገኙ እናምናለን። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር ማግኘት እፈልጋለሁ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ