የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 11/8 ገጽ 22
  • እምነቱ የብርታት ምንጭ ሆኖልኛል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እምነቱ የብርታት ምንጭ ሆኖልኛል
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሁለት አባቶች አንዱን የመምረጥ ፈተና
    ንቁ!—1998
  • መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ከድክመቴ ጥንካሬ ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ይሖዋ ላደረገልኝ ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስጋኝ ነኝ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 11/8 ገጽ 22

እምነቱ የብርታት ምንጭ ሆኖልኛል

አንዲት የ17 ዓመት ልጅ በታኅሣሥ 1998 ንቁ! ላይ ለወጣ ጽሑፍ ያላትን አድናቆት ለመግለጽ የቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ሪፑብሊክ በሆነችው በሞልዶቫ ለሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቢሮ ደብዳቤ ጻፈች። ጽሑፉ “ከሁለት አባቶች አንዱን የመምረጥ ፈተና” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን የአንድን አርመናዊ ወጣት የግል ተሞክሮ የያዘ ነው።

“ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የሕይወት ታሪክ ስላሳለፍኩ ተሞክሮውን በማነብበት ወቅት ዓይኔ ዕንባ አቀረረ” ስትል ገልጻለች። በመቀጠልም እንዲህ ብላለች:- “የ15 ዓመት ልጅ ሳለሁ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት የጀመርኩ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ወላጆቼ አልተቃወሙኝም ነበር። ሆኖም የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ መገኘት ስጀምር ክፉኛ ይቃወሙኝ ጀመር። ከዚያም በ1997፣ የተማርኳቸውን ነገሮች ለሌሎች ማካፈል ስጀምር ወላጆቼ ‘እነዚያ የይሖዋ ምሥክር ጓደኞችሽ ጋር ሂጂ፤ እነርሱው ይቀልቡሽ፣ ያልብሱሽ፣ ሥራም ይስጡሽ። አንቺ በጣም መጥፎ ልጅ ነሽ!’ አሉኝ። አልፎ ተርፎም ወላጆቼ ጭንቅላቴን ከግድግዳ ጋር እያላተሙ ደበደቡኝ።

“ይህ ከባድ ፈተና ሆኖብኝ ነበር። አርመናዊው ወጣት አልፎ አልፎ ይሖዋ ይደሰትብኝ ይሆን እያለ ራሱን ይጠይቅ እንደነበረ ሁሉ እኔም ብዙውን ጊዜ ይኸው ስሜት ይሰማኝ ነበር። ‘ከንቱ ነኝ ማለት ነው? ይሖዋ በፊት ለፈጸምኳቸው ኃጢአቶች ይቅር ይለኝ ይሆን? ይሖዋ ይወድደኝ ይሆን?’ እያልኩ አስብ ነበር።

“በተለይ ይሖዋ አይወደኝም ብዬ ሳስብ ፈተናው በጣም ይከብደኝ ነበር። እርሱን እንዳልተወው እንዲረዳኝና ብርታት እንዲሰጠኝ ከዕንባ ጋር ይሖዋን በጸሎት ተማጽኜዋለሁ። በእርግጥም ይሖዋ ጸሎቴን ሰምቶ ልመናዬን እንደመለሰልኝ ተመልክቻለሁ። ጠንካራ አቋም፣ ጽናትና ድፍረት ሰጥቶኛል። በተለይ ይሖዋ ይህን ያደረገልኝ መዝሙራዊው ‘አባቴና እናቴ ትተውኛልና፣ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ’ ሲል በትምክህት በተናገረበት በቃሉ አማካኝነት ነው።—መዝሙር 27:10

“በመስከረም 27, 1997፣ ካጉል ውስጥ በተደረገ የይሖዋ ምሥክሮች የወረዳ ስብሰባ ላይ በመጠመቅ ለይሖዋ ያደረግሁትን ውሳኔ አሳየሁ። አፍቃሪ የሆነው ሰማያዊ አባታችን ይሖዋ በመዝሙር 84:11 (የ1980 ትርጉም) ላይ የተገለጸውን ‘እግዚአብሔር ጠባቂያችንና ጋሻችን ነው፤ ቸርነትንና ክብርን ያበዛልናል፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም ነገር አይከለክላቸውም’ የሚለውን ቃል የሚፈጽም አምላክ እንደሆነ በግልጽ ማየት ችያለሁ።

“በንቁ! መጽሔት ላይ እምነት የሚያጠናክር የሕይወት ታሪኩን ላካፈለን ለዚያ አርመናዊ ወጣት ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁ። የኋላ ኋላ የኔም ሆኑ የእርሱ ወላጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ፍላጎት እንደሚያድርባቸው ተስፋ አደርጋለሁ።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ